ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት መድረክ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ማህበራትና ልዩ ልዩ ተቋማት እየተሳተፋ ይገኛል።
በኮሚሽኑ የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ዋና አስተባባሪ አቶ ብዙነህ አሰፋ፥ የመድረኩ ተሳታፊዎች ዕድሉን በአግባቡ ተጠቅመው አጀንዳቸውን እንዲያቀርቡና ዜጎች በምክክሩ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ እንዲያቀርቡም ጠይቀዋል።
መድረኩ ሰኞ በሚጀምረው የምክክር መድረክ በንቃት ለመሳተፍና ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎችን ለይቶ ከማዘጋጀት አንጻር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እንዲሁም ምክክሩ ስለሚኖረው ፋይዳ ያላቸውን ግንዛቤና ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።
በመራዖል ከድር