Fana: At a Speed of Life!

የባሕርዳርን ተመራጭነት ሊያጎሉ የሚችሉ መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕርዳር ከተማን ውበት፣ ድምቀትና ሁለንተናዊ ተመራጭነት ሊያጎሉ የሚችሉ መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መለኩ አለበል ተናገሩ፡፡

በአቶ መላኩ አለበል የተመራ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ቡድን በባሕርዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ የኢንዱስት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል÷ ባሕርዳር ለቱሪዝምና ኢንዱስትሪ እድገት ምቹ ከሆኑ ከተሞች መካከል በቀዳሚነት የምትጠቀስ መሆኗን አንስተዋል፡፡

ከተማዋን ሊገልፁ የሚችሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተፋጠኑ ጠቅሰው፤ በተያዘው በጀት ዓመት የተጀመሩ መሰረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የባሕርዳር ከተማን ውበት፣ ድምቀትና ሁለንተናዊ ተመራጭነት ሊያጎሉ የሚችሉ መሰረተ ልማቶች ተገንብተዋል ያሉት ሚኒስትሩ÷ ቀሪ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አመላክተዋል።

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው÷ የከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥ ሊያረጋግጡ የሚችሉ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.