Fana: At a Speed of Life!

አውሮፕላን ማረፊያንና ድንበርን በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አውሮፕላን ማረፊያን እና ድንበርን በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት በተለያዩ ተቋማት መካከል ተደረገ።

ስምምነቱን ያደረጉት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናቸው።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና አገልግሎቱን ለማዘመን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞችም የሚኖራቸውን ቆይታ እንዲያራዝሙ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ ማቅለልና አስተማማኝ ደህንነት እንዲኖር ለማስቻል ስምምነቱ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.