Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሕመድ ሺዴ በሃላባ ዞን የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃላባ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝቱ በሃላባ ዞን ዌራ ጂዶ ወረዳ የሲንቢጣ ቀበሌ ከዚህ በፊት በጎርፍ እና በሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በተረጂነት ትታወቅ እንደነበር ተጠቁሟል።

አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ጸጋ በመለየት ወደ ሥራ በመገባቱ ቀበሌዋ በክልሉ በልማት ሥራ በአብነት የምትጠቀስ መሆኗ ተገልጿል፡፡

አቶ አሕመድ ሺዴ በዞኑ በመስኖ እየለማ የሚገኝ የአትክልትና ፍራፍሬ የልማት ሥራን ተዘዋውረው መመልከታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላሰተር አስተባባሪና ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ መሐመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስና የዞኑ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.