Fana: At a Speed of Life!

የኢትጵዮያ አየር መንገድ ከሁለት ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና ሄናን አቪዬሽን ግሩብ እና ከሺያመን ኢምፖርት ግሩፕ ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራርሟል፡፡

ከቻይና ሄናን አቪዬሽን ግሩብ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሲሆን÷ከሺያመን ኢምፖርት ግሩፕ ጋር የተፈረመው ደግሞ የስትራቴጂክ ትብብር ስምምነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግና በካርጎ ጭነት ዘርፍ የተሳላጠ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላል ተብሏል፡፡

የተፈረሙት ስምምነቶች በፈጠራ ልማት፣ በሃብት መጋራት እና በጋራ ተጠቃሚነት ማዕቀፍ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.