Fana: At a Speed of Life!

169 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 169 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች በሁለት ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው በጂቡቲ ከሚገኘው ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ፍልሰተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የጂቡቲ-የመን መንገድ አደገኛ እና በጀልባ መገልበጥ አደጋ ምክንያት የበርካቶችን ሕይወት ለሞት የዳረገ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ራሱን እና ቤተሰቡን ሊጠብቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.