Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የረጅም ጊዜ ጥበቃና ልማት አስተዳደር አጋርነት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣንና የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የረጅም ጊዜ ጥበቃና ልማት አስተዳደር አጋርነት ስምምነት ከአፍሪካ ፓርክ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

የጋራ ስምምነቱ በመንግስትየግል አጋርነት አስተዳደር ማስተላለፍ የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በሥነ-ሥነርዓቱ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እና የአፍሪካ ፓርክ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.