የሕብረቱ አምባሳደር ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮመስበርገር ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ጋር በሁለትዮሽ ትብብሮች ላይ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው ባሉ የሪፎርም ሥራዎች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ከሕብረቱ ጋር በትብብር ሊሠሩ በሚችሉ መስኮች ላይ መክረዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር ያለማቸውን ዘመናዊ የስማርት ኮርት ሩም የችሎት አዳራሾችን፣ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሠረተ-ልማትን እና ዳታ ሴንተሩን ጎብኝተዋል፡፡