Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እያከናወነ ያለውን ተግባር እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና የኖርዌይ መንግሥት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በትምህርት ዘርፍ እያከናወኑት ያለውን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በክልሉ የትምህርት ጥራትን በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ከኖርዌይ ኤምባሲና ከዩኒሴፍ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ዩኒሴፍ እያከናወናቸው ላሉ ተግባራት ያመሰገኑት ርዕሰ መሥተዳድሩ÷ በቀጣይ የመምህራንን አቅም በማጎልበት፣ የሥርዓተ-ትምህርት ቁሳቁስ ዕጥረትና የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል ላይ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።

የኖርዌይ መንግሥት በክልሉ በሚያከናውቸው የተለያዩ ተግባራት ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ ነን ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የዩኒሴፍ ልዑክ በተቋሙ ድጋፍ የተከናወኑ ሥራዎችን መጎብኘቱን እና በቀጣይም በትምህርት ጥራት ላይ የሚያደርገውን ትብብር እንደሚያጠናክር አረጋግጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.