ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝታቸውም በክልሉ ኩርሙክ ወረዳ በእርሻ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት እና በማዕድን ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተመልክተዋል፡፡
በዚህም በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ መልካም ልምዶችን በመለየት እና ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ በወረዳው የነበራቸውን ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
በቀጣይ ቀናትም መሰል ጉብኝቶችን በሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ላይ እንደሚያከናውኑ ተጠቁሟል፡፡