Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት የተለያዩ ደረጃዎችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት የኢትጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃ አወጣጥና ምደባ አሰራር ተከትሎ የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ደረጃዎች በጥልቀት መርምሮ ማጽደቁ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በ40ኛ እና 41ኛ ስብሰባ ላይ ነው ደረጃዎቹን ያጸደቀው።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በዚህ ወቅት÷ ሁሉም አካላት ደረጃዎቹን እንዲያውቋቸው የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት መስራት እደሚገባ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩትም በምክር ቤቱ አዲስ የጸደቁ ደረጃዎችን ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲያውቋቸው የሚያስችሉ ተከታታይ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.