አቶ አሕመድ ሺዴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዞኑ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ እየለማ ያለ የስንዴ ምርጥ ዘር የልማት ሥራን ተመልክተዋል፡፡
በዞኑ ከ27 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሲሆን÷ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመረውን ጥረት እንደሚያጠናክር ተመላክቷል።
በመስክ ምልከታው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ እና የስልጤ ዞን የሥራ ኃላፊዎችም መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡