2ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት በአዲስ አበባ መስጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት በአዲስ አበባ ከተማ በዘመቻ መስጠት ተጀምሯል።
ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታሕሣሥ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤት፣ በማሳደጊያ ቦታዎች እና በሌሎች ህጻናት በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የፖሊዮ በሽታ የህጻናትን እግር እና እጅ ጡንቻ በማልፈስፈስ ለሽባነት እና ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም እንዲያስከትቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ