ዓመታዊ የጤና ምርምር ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው ዓመታዊ የጤና ምርምር ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባዔውን የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአማራ ክልል ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ጋር በትብብር ማዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡
በዚህ ጉባዔ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የጤና የምርምር ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በጤናው ዘርፍ ምርምር የተደረገባቸው ችግር ፈቺ ጥናቶች ለውይይት ይቀርቡበታል ተብሏል።
በደሳለኝ ቢራራ