Fana: At a Speed of Life!

ሜታ ኩባንያ ለዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት 1 ሚሊየን ዶላር ለገሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት 1 ሚሊየን ዶላር ለግሷል።

 

የገንዘብ ልገሳ የተደረገው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ባለፈው ወር ተመራጩን ፕሬዚዳንት በማራላጎ መኖሪያቸው ከጎበኙ በኋላ ነው ተብሏል።

 

ማርክ ዙከርበርግ በፈረንጆቹ 2020 ከተካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን÷ አሁን ግን ሁሉም ተለውጦ ሁለቱ ሰዎች ወዳጅነት እየፈጠሩ ይመስላል።

 

ማርክ ዙከርበርግ ባለፈው ወር በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት ለእራት ግብዣ በተገናኙበት ወቅት አንዱ ሌላውን ሲያሞካሽም ተሰምቷል።

 

ማርክ ዙከርበርግን ጨምሮ የአፕል አንዲሁም የጎግል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ከአዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ፍላጎታቸውን ያሳዩ ሲሆን÷ የቴስላ ባለቤት ቱጃሩ ኤሎን መስክ ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን እንዲያሸንፉ ከፍተኛ የገንዘብና የምርጫ ቅስቀሳ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል።

 

ለዚህም ዶናልድ ትራምፕ ኤሎን መስክን በፈጠራ የተሞላና ወጪ ቆጣቢ የመንግስት አሰራር ለመዘርጋት የሚያግዝ ተቋም እንዲመሩ መሾማቸው ይታወቃል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.