Fana: At a Speed of Life!

የመቱ -ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 60 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) የተመራ ቡድን የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያን ጎብኝቷል፡፡

ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷አውሮፕላን ማረፊያው ዞኑን የኢንቨስትመንት እና የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

በዞኑ የሚገኘውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በማልማት የህብረተሰቡን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ገልፀዋል፡፡

መሰል የፕሮጀክት ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ ወይም ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድመው እንዲጠናቀቁና ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ጠንካራ ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት።

የፕሮጀክቱ መሐንዲስ አስመላሽ በላይ በበኩላቸው÷የመቱ ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 60 በመቶ መድረሱን ጠቁመው ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.