አቶ መላኩ አለበል በባሕር ዳር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በባሕር ዳር ከተማ ተቋማትንና የልማት ሥራዎችን እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡፡
ሚኒስትሩ ቀደም ብሎ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀመረውን የሪፎርም፣ የቢሮ ዕድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡
በዚህም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ተገልጋይ ህብረተሰብ ጉዳዩን በግልፅ ችሎት እንዲዳኝ እየተከናወኑ ያሉ የችሎት ማስቻያ ስራዎች ሞዴል በሆነ አግባብ እየተሰሩ እንደሆነ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከግቢው ፊት ለፊት የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ በራሱ ወጪ የግንባታና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እያከናወኑ እንደሚገኙ ተመልክቷል።
የከተማው አስተዳደር የከንቲባ ጽህፈት ቤትን መልሶ ማደራጀት ስራንም ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል።
እየተከናወነ ባለው ጉብኝት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው፣ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውና ሌሎች አመራር አባላት ተሳትፈዋል፡፡