Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)  ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዲጂታል ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ማሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

የገንዘብ የክፍያ ሥርዓቱን ማሳለጥ የሚያስችሉ ሁለት አይነት የዲጂል ክፍያ ሥርአቶች በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

QR የተሰኘው ሥርዓት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸውን ተጠቅመው ክፍያ መፈጸም የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሌላኛው የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ደግሞ 3.0 የተሰኘ ሲሆን ÷ለነጋዴዎች የተዘጋጀ እና የክፍያ መንገዶችን የሚያሳልጥ መሆኑን አሪፍ ፔይ አስታውቋል፡፡

አዲሶቹ የዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ደንበኞች የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን የመጠቀም ልምድ እንዲያዳብሩ እና አላስፈላጊ መጉላላትን እንዲያስቀሩ ያስችላሉ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዲጂታል ኢኮኖሚ አውን ለማድረግ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት አንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.