Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከዩክሬን ለተቃጣባት ጥቃት አጸፋ እንደምትሰነዝር ዛተች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ መንግስት ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ አርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም የረጅም ርቀት ሚሳኤል በወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ለሰነዘረችው ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰምትሰጥ አስታወቀች።

 

ሩሲያ ይህንን የገለጸቸው ዩክሬን ትናንት ስድስት ወታደራዊ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም ታጋንሮግ በተባለ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ነው።

 

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ ከተተኮሱት ስድስት ሚሳኤሎች ሁለቱ ተመትተው መውደቃቸውንና ሌሎቹ ደግሞ ኢላማቸውን እንዳይመቱ መደረጋቸውን ገልጿል።

 

በጥቃቱ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን የገለፀ ሲሆን÷ በዩክሬን ለተሰነዘረባት ጥቃት ሩሲያ ተገቢውን የአጸፋ ርምጃ ትወስዳለች ሲልም ገልጿል።

 

የሩሲያን የአጸፋ  ርምጃ በተመለከተ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን “ሩሲያ ባለፈው በዩክሬን የሞከረችው አረሽኒክ የተባለውን ሚሳኤል በመጠቀም ለማጥቃት እንዳሰበች አስታውቃለች” ማለታቸውን ዘድፌንስ ፖስት ድረገፅ ዘግቧል።

ዩክሬን ባለፈው ወር በአሜሪካ ሰራሹ አርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) እና ከእንግሊዝ መንግስት በለገሰው ስቶርም ሻዶው በተባሉ ሚሳኤሎች በሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት መሰንዘሯ ይታወሳል።

 

በምላሹም ሩሲያ አዲስ ሰራሁት ባለችው ኒኩሌር የመሸከም አቅም ባለው ሱፐር ሶኒክ ሚሳኤል ድኒፕሮ የተሰኘች የዩክሬን ከተማን መደብደቧ  አይዘነጋም፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.