Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በቅንጅት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  በቅንጅት እየሰራ መሆኑን  የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

 

“ጥራት ያለው ትምህርት ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ በሲዳማ ክልል 4ኛው የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

 

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በራሲ በየነ በዚህ ወቅት÷የትምህርት ስርዓቱ በአግባቡ ካልተመራ ለሀገር እድገት እንቅፋት ይሆናል ብለዋል፡፡

 

ለዚህም ክልሉ የተለያዩ እቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱንና መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ሁሉን አቀፍ የትምህርት ተሣትፎ በማድረግ ሰፊ ሥራዎች መሰራቱንም ገልፀዋል።

 

በዚህም በክልሉ የትምህርት መነቃቃት በመፈጠሩ ከፍተኛ ወጤት መመዝገቡን አንስተዋል፡፡

 

በመድረኩ  የትምህርት ቤት ምግባ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

 

በጀማል ከዲሮ እና ታመነ አረጋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.