የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉትን ስምምነት እንደሚደግፍ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባወጡት መግለጫ ፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት አድንቀዋል።
ሙሳ ፋኪ ማሃማት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የደረሱበትን ስምምነት በፍጥነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ሀገራቱ ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ላደረጉት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡