Fana: At a Speed of Life!

ስምምነቱ የቀጣናውን ውጥረት ለማርገብ ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ያሳየ ነው -የአውሮፓ ህብረት

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው ስምምነት የቀጣናውን ውጥረት ለማርገብ እርስ በርስ መካበበርና መወያየት አስፈላጊ መሆኑን ያሳየ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት ገለጸ፡፡

ህብረቱ የአንካራውን ስምምነት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷በቱርክ አደራዳሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ህብረቱ በበጎ ጎኑ እንደግፍ አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር የሚያደርግውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ስምምነቱ በምስራቅ አፍሪካ ተከስቶ የነበረውን ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ ንግግር እና እርስ በእርስ መከባበር አስፈላጊ መሆኑን ያሳየ ነውም ብሏል ህብረቱ፡፡

ሁለቱ ሀገራት ወደ ስምምነት እንዲመጡም የቱርክ መንግስት ላደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚመሰገንም ነው ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.