Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ ዓረቢያ ለ2034 ዓለም ዋንጫ 5 ትሪሊየን ዶላር መደበች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ በፈረንጆቹ 2034 ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ 5 ትሪሊየን ዶላር መመደቧ ተገለጸ።

ለውድድሩ 10 ዓመታት የመዘጋጃ ጊዜ ያላት ሳዑዲ ዓረቢያ ከወዲሁ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ተሰምቷል።

ከተግባራዊ እርምጃዎቹ መካከልም አጠቃላይ ዝግጅቱን የሚመራ ከፍተኛ ኮሚሽን መቋቋሙ ነው የተገለጸው፡፡

ለከፍተኛ ኮሚሽኑ የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው እንዲመሩ የተሾሙት ደግሞ የኒው ካስል ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን ሊቀ መንበር ያሲር አል-ሩማያን ናቸው።

ሳዑዲ ለዝግጅቱ ወጪ ከመደበችው 5ትሪሊየን ዶላር በጀት ውስጥ አብዛኛው ለስታዲየሞች ግንባታ ይውላል ተብሏል።

ሀገሪቷ ለውድድሩ ማካሄጃ 15 ስታዲየሞች የሚያስፈልጓት ሲሆን÷ ስምንቱ ገና እንዳዲስ የሚገነቡ መሆናቸው ነው የተጠቀሰው።

ውድድሩን እንደ ኳታር በክረምት ወራት እንደምታስተናግድና ለአየር ሁኔታው የሚስማማ ቅድመ ዝግጅት እንደምታደርግ ዘሽልድስ ጋዜት ዘግቧል።

የዓለም እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ (ፊፋ) የ2030 እና የ2034 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገራትን ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።

በዚህም የ2030 የዓለም ዋንጫን ስፔን፣ አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ እና ፖርቹጋል በጋራ እንደሚያዘጋጁት ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.