Fana: At a Speed of Life!

የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጀት ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጀት ለመገንባት መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ÷ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሃይ እና የሲጂሲኦሲ ግሩፕ በተገኙበት የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን በፍጥነት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ2008 ዓ/ም ከኤግዚም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ይገነባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ብድሩ እስከ ዛሬ ባለመለቀቁ ምክንያት ሳይጀመር በመዘግየቱ የከተማው አስተዳደር በራሱ በጀት ለመገንባት ወስኗልም ነው ያሉት፡፡

በከተማዋ ያለውን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ በራሱ በጀት ለመገንባት ዛሬ ከቻይና ኤምባሲ እና ከኮንትራክተሩ ሲጂሲኦሲ ግሩፕ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የከተማዋን የውሃ አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ነው ከንቲባዋ ያነሱት፡፡

የፕሮጀክት ግንባታው ሲጠናቀቅ ይህንን ጥረታችንን ይበልጥ ውጤታማ እንደ ሚያደርግና ያለብንን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይበልጥ እንደሚፈታ እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.