Fana: At a Speed of Life!

ያለንን የተፈጥሮ ፀጋና ሰብዓዊ ሀብት ስራ ላይ በማዋል የህዝባችንን ህይወት እናሻሽላለን -ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ያለንን የተፈጥሮ ፀጋና ሰብዓዊ ሀብት ስራ ላይ በማዋል የህዝባችንን ህይወት እናሻሽላለን ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ የበጋ ስንዴ ልማት ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦር ዞን አመርቂ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተዟዙረን እንደተመለከትነው ግብርናችንን በማዘመን፣ ከሞፈርና በሬ በማላቀቅ ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ አለብን ተብሎ የተያዘውን ግብ በሚያሳካ መንገድ በተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት ተስፋችን ለምልሟል ብለዋል።

እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን እናረጋግጣለን ያሉት ተስፋዬ (ዶ/ር፥ ከተመፅዋችነት ነፃ እንወጣለን ፣ በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን እያረጋገጥን እንሄዳለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ያለንን የተፈጥሮ ፀጋ እና ሰብዓዊ ሃብት ስራ ላይ በማዋል የህዝባችንን ህይወት እናሻሽላለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ከፍታ የማረጋገጥ ትልሞች እውን ማድረግ እንደሚቻል ፤ ከፍታ ምኞት ሳይሆን ተጨባጭነቱ መሬት ላይ በሚሰሩ ስራዎች እየተረጋጋጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.