Fana: At a Speed of Life!

የጽናቷ ከተማ የአፍሪካ እምብርት – አዲስ አበባ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የትምህርት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ቡሳኒ ንግካዌኒ ስለአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ በዴይሊ ማቭሪክ ከትበዋል፡፡

አዲስ አበባ እንደደርባን፣ ሉዋንዳ ሞምባሳና ኪንሻሳ የእድገት መልክ፣ ተስፋም ተስፋ ቆርጦ ተኖ የሚጠፋባት ከተማ ናት ይሏታል ዳይሬክተሩ በጽሁፋቸው፡፡

ዙሪያዋን በተፈጥሮ ተራራ የምትጠበቀዋን መዲናቸው ሲያሞጋግሱ የእውቅዋ ባለድምጸመረዋዋን የትሬሲ ቻፕማንን የሙዚቃ ቃላትን በመዋስም ነው፡፡

”ሎስት ቱ ማተርስ ኦፍ ኽርት” ሲሉም ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በፍቅር መውደቃቸውን ሳያንገራግሩ ይገልጹላታል፤ ግዴታ ሆነና መነጣጠላችን እስክንገናኝ ድረስ አበባሽ ይበልጥ ፈክቶና አብቦ ይቆየኝ ሲሉም የልባቸውን ከተማ ይሰናበታሉ፡፡

ለውጧ ጉልህ መሆኑን የሚመሰክሩላት ቡሳኒ ንግካዌኒ ከተማዋ እንደስሟ ስታብብ የመታደስ ስሜትን የሚያጎናጽፍ ኃይል አላት ይላሉ፡፡ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በመመልከት መደነቃቸውንና ወደየስማርት ከተማነት የምታደርገውን ጉዞ እንደሚያጋልጥባት ይናራሉ፡፡

በዚህ ሁሉ የአዲስ አበባ ጥንቁቅ አስተዳደር ከመደነቅ በቀር ምንም ማድረግ አይቻልም፤ ከአውሮፕላን ማረፊያው እስከ ከንቲባዋ ቢሮ ድረስ ከተማዋ የስርዓት እና የዓላማ አየር ይነፍስባታል፡፡

ብርቱካናማ ቱታ የለበሱ የከተማዋ የጽዳት አለኝታዎቿ ውበቷን ለመግለጥ ትጋታቸው የሚነበብ ነው፤ ከእያንዳንዱ የአስፋልት ስር አዳዲስ የውሃ ቱቦዎችና የፋይበር ኦፕቲክ ኬብሎች በመዘርጋት የከተማዋን እድገት ለማስቀጠል የደም ስር ይሆኗታል ይላሉ በከተቡት ጽሁፍ፡፡

የእግረኛ መንገድ እና ሳይክል መንገዶች የትራፊክ መብራቶች እና አደባባዩዎችንም ያነሳሉ፤ ይደነቃሉ፡፡

አዲስ አበባ ከከተማ በላይ ናት፣ አዲስ ምልክት የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሞገሳም አስተናጋጅ ናት ሲሉ ይገልጿታል፡፡

መዲናዋ መነሻቸው እልፍ የሆኑ ህዝቦቿን አቅፋ፤ ልዩነታቸውን አቻችላ በፍቅር የምታኖር ናት እንደዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፡፡

ከዓለማችን ማዕዘናት የመጡ ዲፕሎማቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ፤ የከተማዋ የጥበብ ውብ ሸራ ልባቸው ላይ ስትስል ያለርህራሄ መሆኑንም ይገልጣሉ፡፡

በአጀንዳ 2063 ለሁሉም አፍሪካውያን የስራ እድል እና ብልጽግና የሚያመጣውን ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ልማት ለማፋጠን የጋራ ውሳኔ እንዳለም ይጠቁማሉ፡፡

አዲስ አበባ ከመሰብሰቢያነት በላይ ናት፤ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ህልሞች የሚቀረፁበት የአንድነት መድረክም ናት ይሏታል፡፡

አዲስ አበባ እንደ ስሟ ዘመንን የምትሻገር አበባ ናት፥ የአበባ ጉንጉኖቿ ንቁ እና ህይወት ያላቸው ለመጥለቅ ፈቃደኛ ያልሆነችውን የአፍሪካ ከተማ ታሪክ ይነግራሉ፡፡

በዘመናዊነት እቅፍ ውስጥ ሥሯን በማጠንከር ዘመናዊነትን ከባህላዊው ጋር የማጣጣሚያ መንገዶቿን ስታስስ አለች፡፡

ፀሐይ በአዲስ አበባ ጎዳናዎ በማብራት ለመላው አፍሪካ የተሻለ ነገን ታበስራለች፤ በንፁህ አስፋልቶቿ፣ በግሩም የመንገድ ብርሃኖቿ፣ በዘንባባ ዛፎቿ፣ በማይቦዝነው የትራፊክ እንቅስቃሴዎቿ፣ በዋህ ህዝቦቿ እና ተስፋወቿ በከተማዋ ብቻ አይገደብም ሲሉ ተቀኝተውላታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.