አሜሪካ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉትን ስምምነት እደግፋለሁ አለች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉትን ስምምነት እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡
አሜሪካ በትናትናው ዕለት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት የሀገራቱን ሉዓላዊነት በጋራ ጥቅሞች ላይ የሚደረግን ትብብር መሰረት ያደረገውን ስምምነት እንደምትደግፍ ገልጻለች፡፡
በዚህም ሂደት ላይ ጉልህ ሚና የተጫወተውን ቱርክን አመስግናለች፡፡
የሶማሊያን የግዛት አንድነት በማክበር ለጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን ሚያስችለውን ተግባራዊነት እንጠብቃለን ብላለች፡፡
ቀጣይነት ያለው ውይይት እና ተሳትፎ ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የወደፊት መረጋጋትና ብልጽግና አስፈላጊ መሆናቸውንም አሜሪካ ጠቁማለች፡፡
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በጋራ የጸጥታ ጉዳዮች በተለይም አልሸባብን በመዋጋት ላይ ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ እናበረታታለን ለች አሜሪካ ፥ ከሁለቱም ሀገራት ጋር ያለኝን የጠበቀ የሁለትዮሽ ትብብር እቀጥላለሁ ብላለች።