አቶ ሽመልስ አብዲሳ በባሌ ዞን አገርፋ ወረዳ በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በባሌ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎቸን እየጎበኙ ነው፡፡
በዛሬው ዕለትም በዞኑ አገርፋ ወረዳ በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አቶ ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የባሌ ዞን በግብርና፣ ቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች እምቅ አቅም ያለው አካባቢ ነው፡፡
ስለሆነም ከተለመደው አሰራር በመውጣት የሕዝቡን ተጠቃሚነት በሚገባ ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት፡፡
አርሶ አደሩ የተሻለ ሕይወት እንዲመራም አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል፡፡