Fana: At a Speed of Life!

ለከተሞች የቱሪዝም መነቃቃት የኮሪደር ልማት ስራዎች የላቀ ፋይዳ አላቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በከተሞች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሞችን ለስራና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባሻገር የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆኑ የላቀ ፋይዳ እንዳላቸው የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።

ሚኒስትሯ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀዋሳ ከተማ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን የኮሪደር ልማት ስራን በጎበኙበት ወቅት÷ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ማየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

ሀዋሳ በርካታ የቱሪስት መስህብ ስፍራ ባለቤት መሆኗን ጠቁመው፤ የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ውበትን እንዳላበሳትም ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ከተሞችን ለስራና ለኑሮ የተመቹ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የኮሪደር ልማት ስራው ፋይዳ የላቀ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሯ ከሀዋሳ የኮሪደር ልማት በተጨማሪ የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴን የተመለከቱ ሲሆን÷ በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልልና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.