የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያና ሶማሊያን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል በአንካራ የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት እንዳለው ፥ ስምምነቱ በወዳጅነት እና በእርስ በርስ መከባበር መንፈስ የመጣ እንደሆነም ገልጿል፡፡
በዚህም የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊነት እውን እንደሚሆን የጠቆመ ሲሆን ፥ ለዚህም ስምምነት ትልቁን ድርሻ የተወጣቸውን ተርኪዬን አመስግኗል፡፡
በዚህም የስምምነቱ ትግበራ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅሶ ፥ ልዩነቶች በንግግር ለመፍታት የፖለቲካ ፍቃደኝነት እንደሚያስፈልግም ነው የተጠቆመው፡፡
በተመሳሳይ ብሪታኒያ ስምምነቱ የኢትዮጵያን እና የሶማሊያን በጋራ የመልማት ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ያሳየ ነው በማለት ስምነቱን እንደምትደግፍ የገለጸች ሲሆን ፥ የትርክዬን ሚናም አድንቃለች።
ብሪታኒያ በቀጣናው መረጋጋት፣ ልማት እና ሰላም እንዲሰፍን ከሀገራቱ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም አስታውቃለች።