Fana: At a Speed of Life!

550 ሺህ ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል 550 ሺህ ኩንታል ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡

በቅርብ ቀናትም 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ዳፕ የጫኑ አራት መርከቦች ወደብ እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡

ለዘንድሮ የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ወደብ መድረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመልክቷል፡፡

ከዚህ ውስጥም ከ472 ሺህ 210 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ነው የተጠቆመው፡፡

የግብርና ሚኒስቴር በየዓመቱ እያጠና በሚያቀርበው የሀገሪቱ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሰረት ኮርፖሬሽኑ ዓለም አቀፍ ጨረታ እያወጣ የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ላይ ይገኛል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.