በደሴ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው- ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በደሴ ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ ዘርፈ-ብዙ የልማት ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ደሴን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን የቴክኖሎጂ ሥራ ሂደት፣ የሌማት ትሩፋት እና የኮሪደር ልማት ተግባራትን ተመልክተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም ከተማ አሥተዳደሩ በርካታ ሥራዎችን በሕብረተሰቡ ተሳትፎ እያከናወነ መሆኑን በጥሩ ተሞክሮ ተመልክተናል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ሥራዎች በተጀመሩበት ፍጥነት እንዲጠናቀቁም መንግሥት የማያቋርጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
በኢሌኒ ተሰማ