Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር እና ዩኒሴፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በግጭት መከላከል እና በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ዘላቂ ሰላም ለመገንባት፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ፣ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገዋል፡፡

አቡበከር ካምፖ(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ከመገንባት አኳያ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ከተቋማቸው ተልዕኮ ጋር የሚናበብ መሆኑን መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት በግጭት መከላከል እና በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.