አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ።
በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ሰላም፣ ልማትና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘሪያ ለጋራ ምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አባላት በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄዱ የሚገኙ የልማትና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ መረጃ አመልክቷል።