ከንቲባ አዳነች ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ግንባታን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የበጎነት መንደር ውስጥ በመገንባት ላይ ያሉ ሁለት ባለ ዘጠኝ ወለል የመኖሪያ ቤት ሕንጻዎችን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡
በመንደሩ እስከ አሁን ሰባት የመኖሪያ ሕንጻዎች ግንባታ ተጠናቅቆ ለልማት ተነሺዎች እና በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ የኑሮ ጫና ላለባቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች መተላለፉን ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
በመኖሪያ መንደሩ ለሚገኙ ነዋሪችም የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ዕድሎች መፈጠሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
በከተማ አሥተዳደሩ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር እየተገነቡ ያሉትን ሁለት ባለ ዘጠኝ ወለል የመኖሪያ ቤት ሕንጻዎች በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑም አመላክተዋል፡፡