Fana: At a Speed of Life!

የአንካራው ስምምነት የብልፅግና ጉዟችንን ከፍ አድርጓል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንካራው ስምምነት እንደ ሀገር የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ በሐረሪ ክልል ከአመራሩ ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት÷ ስምምነቱ ከጦርነት እና ብጥብጥ ይልቅ ሀገራችንን ወደ ዘላቂ ሰላም የሚወስድ ብሎም ወንድማማችነትን የሚያጎለበት ነው፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ልማት እና ብልፅግና የማይፈልጉ ባገኙት አጋጣሚ ሀገራችንን ወደ ጦርነት አውድማ ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታሪካዊ ጠላቶችን አንገት ያስደፋ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ከባሕር በር ጥያቄው ጎን ለጎን በተጀመሩ የመልካም አሥተዳደር እና የልማት ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ርብርብ ያደርጋል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.