Fana: At a Speed of Life!

በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ ሥራዎች ተከናውነዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ በሆኑት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናል ብለዋል።

ማዕከሉ ወላጆቻቸውን ላጡ እና በችግር ውስጥ ያሉ ሕጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.