Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 1 ሺህ 314 የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች አገልግሎት እየሠጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዓመታት 1 ሺህ 314 የሕጻናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው 15ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ መካሄዱን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማችንን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በርካታ ስራዎች ሠርተተናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም 1 ሺህ 314 የሕጻናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናል ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በሁሉም ክፍለ ከተሞቻችን 128 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና መርሐ-ግብሮችን ከፍተን እሠራን ነው ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ የስፖርትን ጥቅም በመገንዘብ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.