Fana: At a Speed of Life!

የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው – አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለፁ።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተገኙበት የውይይት መድረክ  ተካሄዷል።

በውይይት መድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ስምምነቱ ለቀጠናው ሰላም እና የኢኮኖሚ ውህደት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የባህር በር ለማግኘት እውቅና መሰጠቱ መንግስት በዲፕሎማሲው መስክ ያመጣው ስኬት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት አመራሮች በበኩላቸው ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ የበኩላችንን እንወጣለን ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.