Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የማንቼስተር ሲቲ ተጨዋች ሚካይል ኬቬላቪሊ የጆርጂያ ፕሬዚዳታዊ ምርጫን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ እና ሌሎች ክለቦች በእግርኳስ ተጫዋችነት ያሳለፉት ሚካይል ኬቬላቪሊ የጆርጂያ ፕሬዚዳታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ተገለፀ፡፡

የ53 አመቱ ጎልማሳ ከ300 የሀገሪቱ ፓርላሜንታዊ የምርጫ ድምፅ 224 በማሸነፍ ነው የተመረጡት፡፡

ኬቬላቪሊ ፒፕልስ ፓዎር ተባለውን የፖለቲካ ፓርቲ በመቀላቀል ወደ ፖለቲካው ብቅ ያሉ ሲሆን ፓርቲያቸው ከገዥው የጆርጂያን ድሪም ፓርቲ ጋር መቀላቀሉን ተከትሎ በውህድ ፓርቲው ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ጆርጂያን ድሪም ፓርቲ ባደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ኬቬላቪሊ ማግኘት ከሚጠበቅባቸው 200 ድምፆች በላይ በማግኘት የጆርጂያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳሎም ዞርቢችቪሊን በመተካት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንተ መሆን ችለዋል።

ሚካይል ኬቬላቪሊ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመናቸው በእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ፣ በስዊዘርላንድ ደግሞ ግራስሆፐር፣ ዙሪክ፣ ሉዘርን፣ ሲዮን፣ አራሁ እና ባዝል ክለቦች ተጫወተዋል።

ለሀገራቸው ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 46 ጊዜ ተሰለፈው መጫወታቸውን አር ቲ እና ዘጋርዲያን ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.