ሊቨርፑል እና አርሰናል ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር መሪው ሊቨርፑል እና አርሰናል ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ተለያይተዋል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአንፊልድ ፉልሃምን ያስተናገደው ሊቨርፑል 2 አቻ ሲለያይ፤ ኮዲ ጋክፖ እና ዲያጎ ጆታ ለሊቨርፑል እንዲሁም አንደሪያስ ፔሬራ እና ሮቤርቶ ሙኒዝ የፉልሃም ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የሊቨርፑሉ አማካይ አንዲ ሮበርተሰን በሜዳ ላይ በፈፀመው ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡
በተመሳሳይ በኤሚሬትስ ኤቨርተንን ያስተናገደው አርሰናል ያለምንም ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡
እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ሌስተርን ሲቲን 4 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ኢፕስዊች ዎልቭስን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡