Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የሚያስተላልፈው የኃይል አቅርቦት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ፣ የኬንያና የታንዛንያ የሀይል መሰረተ ልማት አካል የሆነው ኃይል ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የሚያስተላልፈው መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት ጀምሯል፡፡

 

የፕሮጀክቱ የመጀመሪያው የኃይል ትስስር በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል የተፈጠረ ሲሆን÷ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በተዘረጋው የኃይል አቅርቦት መሰረተ ልማት በኩል የኃይል ትስስሩ እውን መሆን መቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

 

ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን ያመጣል ተብሏል።

 

የኃይል ትስስሩ ኢትዮጵያ ያላትን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማስፋፋት የአረንጓዴ የኤሌክትሪክ ኃይል ግብይትን በቀጣናው እንዲስፋፋ ሚና እንድትጫወት የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።

 

ኢትዮጵያ በመጀመሪያዎቹ የግብይት ዘመናት በዓመት ከ200 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገቢ እንድታገኝ እንደሚያስችላት የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

 

ለፕሮጀክቱ የአለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የፈረንሳይ የልማት ፋይናንስ ተቋም ድጋፍ አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.