Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አቀፍ የኮሪደር ልማት እና የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ፣ የሀድያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር በክልሉ ሰባት የክላስተር ማዕከል ከተሞች በድምሩ 165 ኪሎ ሜትር መንገድ ለማልማት መታቀዱ ተጠቁሟል።

በመርሃ-ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው በከተማው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነ የህዝብ መድኃኒት ቤት ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ እንደሚያስቀምጡም መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.