Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 22 ፍልስጤማውያን መሞታቸው ተገለጸ።

በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዲር አል ባላህ ከተማ በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት ህንጻ አቅራቢያ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።

በጥቃቱ የከተማዋ ከንቲባ የሆኑት እና በማዕከላዊ ጋዛ የሃማስ አስተዳደር ኮሚቴ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብም መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የእስራኤል ጦር ከንቲባው የጥቃቱ ኢላማ እንደነበሩ ገልጾ የሃማስ ወታደሮችን ይደግፉ ነበር ብሏል።

በአካባቢው በተፈፀመ ሌላ ጥቃት አራት ተጨማሪ ሰዎችም ተገድለዋል።

እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የእስራኤል አውሮፕላኖች ታጣቂዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ኢላማ ለማድረግ በእርዳታ መስጫ መጋዘን አቅራቢያ ጥቃት መፈጸማቸውንም ዘገባው አካቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.