Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ነገ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ ይጀምራል።

 

በመድረኩ ከክልሉ 356 ወረዳዎች የተመረጡ ከ7 ሺህ 500 በላይ የህብረተሰብ ወኪሎች በ4 ቡድኖች ተከፍለው የሚመክሩ መሆኑን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ(ፕ/ር) ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

 

ዋና ኮሚሽነሩ እንዳሉት÷በዚህ ክልላዊ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ላይ አምስት የህብረተሰብ ክፍሎች፣ 7 ሺህ 20 የህብረተሰብ ወኪሎች፣ 1 ሺህ 700 የክልሉ ባለድርሻ አካላት፣ 48 ሞደሬተሮች ፣ 350 ድጋፍ ሰጭ ተባባሪ አካላትና 150 በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.