Fana: At a Speed of Life!

ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ የኩርስክ ግዛትን ለመያዝ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን አሰማርታለች አሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ሩሲያ በኩርስክ ግዛት የዩክሬን ቦታዎችን ለመቆጣጠር የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን ማሰማራት ጀምራለች ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ተናገሩ።

 

ሩሲያውያን እነዚህን ወታደሮች በጦራቸው ውስጥ በማካተት በኩርስክ ግዛት ውስጥ በሚያደርጓቸው ውጊያዎች እየተጠቀሟቸው ይገኛሉም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

 

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ “ዛሬ ሩሲያውያን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን በአውደ ውጊያዎች መጠቀም እንደጀመሩ ተጨባጭ መረጃ አግኝተናል፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ነው” ሲሉ ማስታወቃቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

 

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ፒዮንግያንግ ሩሲያን ለመርዳት ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወታደሮችን ልካለች በሚል ሲከሱ ቆይተዋል።

 

በሌላ በኩል የሩሲያ ባለስልጣናት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በምዕራብ ኦሪዮል ክልል የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ለማስቆም ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል።

 

የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለሩሲያ ወታደሮች የነዳጅ አቅርቦት ዋና ምንጭ በሆነው በሩሲያ ኦሪዮል ክልል በሚገኝ የነዳጅ ጣቢያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የዩክሬን ጦር ማስታወቁ አይዘነጋም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.