Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሕርዳር ከተማ “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት ተካሄዷል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷በከተማው በተከናወነ የሰላም ማስክበር ስራ ሰላምን ማስፈን ተችሏል።

አሁን በከተማዋ ሰላምን በዘላቂነት በማጽናት ወደ ተሟላ ልማት ፊታችን የምናዞርበት ወቅት ላይ ደርሰናል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የክልሉና ከተማ አመራር አባላት በፖለቲካው መስክ በርካታ ህዝባዊ ውይይቶችን ማካሄዳቸውን አውስተው÷በፀጥታ ሃይሉና በህዝቡ የተቀናጀ ስራ የተገኘ የሰላም ድል መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በተገኘው ሰላም የከተማዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴ የሚያሻሽሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

የልማት ስራዎቹ የከተማዋን ዘላቂ እድገት ከማረጋገጥ ባለፈ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን ማጠናከር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነም አመልክተዋል።

የተገኘውን ሰላም በመላ ህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገርና ለማጽናት በትኩረት እንደሚሰራ አጽንኦት መስጠታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.