Fana: At a Speed of Life!

የአንካራው ሥምምነት ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ድል ያሥመዘገበችበት መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንካራው ሥምምነት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ድል ያሥመዘገበችበት መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

ሥምምነቱ ለቀጣናው መረጋጋትን እንደሚፈጥርም ነው የምክር ቤቱ ፀሐፊ ደሥታ ዲንቃ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የገለጹት፡፡

በሌላ በኩል ከሶማሊያ ጋር የነበረውን አለመግባባት ተጠቅመው የኢትዮጵያን የውሥጥ እና ውጫዊ የሠላም እና ልማት እንቅሥቃሴዎች ለማወክ ለቋመጡ ኃይሎች ኪሣራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጉዳዩን በትኩረት ሲከታተለው እንደነበር አንስተው÷ አሁን በተደረሠው ሥምምነት ደሥተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም ለሶማሊያ ሠላምና መረጋጋት ከፍተኛ ዋጋ ለከፈለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሥምምነቱ ዋጋው ብዙ ነው ብለዋል።

በሰለሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.