Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ያዘጋጀዉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

 

ከዛሬ  ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደዉ የምክክር መድረክ ላይ ከክልሉ 356 ወረዳዎች ከ10 የማህበረሰብ መሰረቶች የተመረጡ ከ7 ሺህ በላይ  የማህበረሰብ ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በምክክር ይለያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ምክክር የሚካሄድ ሲሆን÷ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ 1ሺ 700 የክልል ባለድርሻ አካላት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በክልሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ተመካክረው ያደራጃሉ።

 

በክልሉ በሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ 48 ሞደሬተሮች (መምህራን) ውይይቶቹን የሚያስተባብሩ ሲሆን÷ 356 የክልሉ ተባባሪ አካላትም ለሂደቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

 

ከ100 በላይ የኮሚሽኑ ሰራተኞችና 150 በጎ ፈቃደኛ የዩንቨርስቲ ተማሪዎችም ሂደቱን በተለያየ መልኩ ያግዛሉ፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ(ፕ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ዘላቂና መሰረት ያለው መፍትሄ ለማምጣት ምክክሩን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁሉም ህዝቦች የሀገራችሁ ጉዳይ ያገባቹሀል ተብለው መሰባሰባቸው ምክክሩን ልዩ እንደሚያደርገው ጠቅሰው ይህንን ማሳካት ደግሞ የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በመራኦል ከድር

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.