ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ከእስራኤል ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ከእስራኤል ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የእስራኤል ባለሃብቶች በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉብት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የአማራ ክልል ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም ያለው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸው ተጠቁሟል፡፡
የእስራኤል ባለሃብቶችም ክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ተጠቅመው ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡